- የትምህርትና ስልጠና የስራ ቡድን የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
- የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት፤ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
- ለትምህርትና ስልጠና አሰጣጥ የሚዉሉ ሰብዓዊ የግብዓት አቅርቦት፤ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
- የስልጠና እድል ሊያሰፉ የሚችሉ አሰራሮችን በመጠቀም የአቀባበል መመሪያ ማዘጋጀትና ለአፈፃፀሙ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
- የስልጠና ትግበራዉንና ምዘናዉን መከታተልና መደገፍ፤
- የስልጠና ግብዓት ደህንነትን መጠበቅና ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
- የሰልጣኞችን መረጃ መያዝ ለአፈፃፀሙ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
- ሰልጣኞች በተመረቁበት ሙያ ስራ እንዲይዙ የሚያስችል ስራ ማከናወን፤
- የድህረ ስልጠና ጥናት ማካሄድ፤
- በኮሌጁ ለሚሠጠው ስልጠና የሚያስፈልገውን የስልጠና ኘሮግራምና የተለያዩ ሞጁዩሎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣
- ወደ ስልጠና ሙያ ሊደለደሉ ስለሚገባቸው ሠልጣኞች የስልጠና ዓይነት መስፈርቶችን በማዘጋጀት ለተቋማት ያቀርባል፤
- የማክማማ/ማህበረሰብ ክህሎት ማሰልጠኛ ማዕከላትን/ያስተዳድራል፤ይከታተላል፤
- የስልጠና ሙያዎችን የሚመለከቱ የስልጠና ችግሮች የሚፈቱበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
- የትብብርና የኩባንያ ስልጠና መርሃ-ግብር በተነደፈለት ስልት መሠረት እንዲፈፀም ያስተባብራል፤ተግባራዊነቱን ያረጋግጣል፡፡
- በቴ/ሙያ ስልጠና ዘርፍ ለተሰማሩና መሰማራት ለሚፈልጉ የሙያ ምክር አገልግሎትና መረጃ ይሰጣል፤
- መንግስታዊ ላልሆኑና ለግል ባለሀብቶች በመካከለኛ ደረጃ ስልጠና ለመጀመር የሚያስችል ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
- ለግል ባለሀብቱ በዝቅተኛና መካከለኛ ደረጃ መደበኛ ያልሆነ አጫጭር ስልጠና ፈቃድ ይሰጣል፤ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
- ግንዘቤ የተፈጠረላቸው የተደራጁ ኢንትርፕራይዞች በብቃትና በጥራት ስልጠና ይሰጣል፤ከስልጠና በኋላ በተሰማሩበት መስክ ውጤታማ መሆናቸውን ይከታተላል፤